ስለ እኛ

ስለ እኛ

ናኖ የዱቄት ቀለም ካርትሬጅ ናኖዳስ ትሬድ ኤንድ ኢንደስትሪ ፒኤልሲ በተባለ በ2002 ዓ.ም በሀገር በቀል ባለሐብቶች በተቋቋመ ኩባንያ በኢትዮጵያ የሚመረት ምርት ነው.

ፋብሪካችን በኦሮሚያ ልዩ ዞን በ5000 ሜትር ስኩዌር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን ከ1000 በላይ ሰራተኞች አሉት። ፋብሪካው በልዩ ማሽኖች እና የዱቄት ቀለም ካርትሬጅ በመገጣጠም በአግባቡ በሰለጠኑ ቴክኒሻኖች የተሟላ ነው

የምርቶች የዓይነት ብዛት

የካርትሪጆቻችን፣ የቀለሞቻችን እና የማስተር ዓይነቶች ብዛት ከፍተኛ ነው ብለን የምናስብበት ምክንያት አለን- ከዋነኛ ተወዳደሪያችን አቅም ከ75% በላይ የበለጠ!

ነፃ ጥገናዎች

ምርቶቻችንን ለሚገዙ ደንበኞቻችን ሁሉ የ18 ወር ዋስትና እንሰጣለን። ሁሉንም ዓይነት ጥገናዎች ያካተተ።

18 ወራት

ገበያ ላይ ጥራት ያላቸው ምርቶች የሉም ወይም በውድ እና በርካሽ ምርቶች መካከል ልዩነት የለም ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል፤ ምርጥ ካርትሪጆችን በርካሽ ዋጋ እናቀርብልዎታለን!

የምርት ክምችት

%

በድጋሚ የሚመጡ ደንበኞች

ጠያቂዎች

የጥራት ቁጥጥር እና ፅኑነት

የጥራት ቁጥጥር እና ፅኑነት

ለሁሉም ሂደቶቻችን፣ ምርቶቻችን እና አገልግሎታቸን ጥብቅ የሆነ የጥራት ቁጥጥር አለን። እየንዳንዱ የዱቄት ቀለም ካርትሪጆች፣ ቀለሞች እና ማስተር የሚመረቱት ከጥሬ እቃ አመራረጥ ጀምሮ እስከመጨረሻው ሙከራ ባለው የምርት ሂደት ሁሉ በሚደረግ ጥብቅ የጥራት ቁጥጥር ነው’ ይህም የዱቄት ቀለም ካርትሪጆቻችን እና ቀለሞቻችን ለከለር፣ ጥራት እና ፅኑነት የሚያመጡትን ፍፁም ብቃት ያረጋግጥልናል።

የምርት እና ክምችት ብቃት

የምርት እና ክምችት ብቃት

በአሁኑ ሰዓት ናኖዳስ በየቀኑ1000 የማተሚያ ማሽን፣ የፎቶ ኮፒ እና የፋክስ የዱቄት ቀለም ካርተሪጆች ቀለሞችን እና ማስተር ማምረት የሚችል ሲሆን ይህም ለእነዚህ ምርቶች እያደገ ያለውን የገበያ ፍላጎት ማርካት ያስችላል። በአሁኑ ሰዓት ከ120,000 በላይ የተለያየ ዐይነት ያላቸው የማተሚያ ማሽን፣ የፎቶ ኮፒ እና የፋክስ የዱቄት ቀለም ካርተሪጆች ክምችት ያለን ሲሆን አሁን ካለው የገበያ ፍላጎት ጋር ለማመጣጠን ሲባል በቅርብ ጊዜ ውስጥ በእጥፍ ያድጋል።

ተመጣጣኝ ዋጋ እና ዋስትና

ተመጣጣኝ ዋጋ እና ዋስትና

ሁልጊዜም ቢሆን በሁሉም ምርቶቻችን እና አገልግሎታችን የተሻለ፣ ተመጣጣኝ እና ተፎካካሪ ዋጋ ለማቅረብ እንተጋለን። በ24 ሰዓታት ውስት ምላሽ የሚሰጥ ተሸላሚ የደንበኞች አገልግሎት። በደንበኞች አገልግሎት፣ በችግር አፈታት፣ በአሻሻጥ ጥበብ እና በማድረስ የካበተ ልምድ አለን’ በሁሉም ምቶቻችን ብቃት እና እርካታ 100% ዋስትና እንሰጣለን።

የምርቶች ዓይነት ብዛት

የምርቶች ዓይነት ብዛት

ናኖዳስ ከ250 በላይ የህትመት ቀለም ሞዴሎችን እንደየፍላጎትዎ ያቀርባል። የተለያየ ዓይነት ያላቸው ምርቶችና አገልግሎቶች በአንድ በናኖዳስ ያገኛሉ። ፋብሪካችን በኦሮሚያ ልዩ ዞን በ5000 ሜትር ስኩዌር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን ከ1000 በላይ ሰራተኞች አሉት። ፋብሪካው በልዩ ማሽኖች እና የዱቄት ቀለም ካርትሬጅ በመገጣጠም በአግባቡ በሰለጠኑ ቴክኒሻኖች የተሟላ ነው።