ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች (ተየጥ)

ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች (ተየጥ)

መልቲ ፈንክሽን ፕሪንተር ምንድን ነው?

መልቲ ፈንክሽን ፕሪንተር (አንዳንድ ጊዜ ኤምኤፍፒ ተብሎ ይጠራል) ፎቶ ኮፒን፣ ስካነርን እና ፋክስ ማሺንን እንዲሁም ማተሚያን በአንድ ራሱን ችሎ የሚቆም ወይም ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ መሳርያ በአንድ ላይ አድርጎ የሚይዝ ማሺን ነው። እነዚህ ሁሉንም የህትመት ፍላጎትዎን በአንድ ቦታ እንዲያገኙ የሚጥሩ ቦታን እና ሃይልን የሚቆጥቡ ማሺኖች ናቸው።

ስታንድ አሎን(ለአንድ ተግባር የተወሰነ) የፎቶኮፒ/ማባዣ ማሺን ምንድን ነው?

ስታንድ አሎን የፎቶ ኮፒ/ማባዣ ማሺን ማለት ሙሉ በሙሉ ለማባዛት አገልግሎት ብቻ የሚውል ቁስ ነው። ይህ የፎቶ ኮፒ/ማባዣ ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት ማባዛት፣ ትልቅ እና ወጪ ቆጣቢ ቀለሞች፣ እንደ ወረቀት ማያያዝ፣ መለበድ፣ የመለየት እና በመጠን የማስቀመጥ ያሉ የወረቀት አያያዝ ዘዴዎች፣ የተለያየ መጠን ባላቸው ወረቀቶች ማዘት መቻል፣ በአንድ ገፅ ብዙ ማተም እና ብዛት ላለው ስራ ጠንካራ ሃይል ይገኙበታል።

በኢንክ ጄት እና በሌዘር ጄት ማተሚያዎች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

የኢንክ ጀት ማተሚያ ተከታታይ የሆኑ ጥቃቅን ነጠብጣቦችን ወረቀቱ (የሚታተምበት ነገር ላይ) ፈሳሽ ቀለም በመርጨት ይጠቀማል። በኢንክ ጄት እና በሌዘር ጄት ማተሚያዎች መካከል ያለው ግልፅ ልዩነት አንድ ምስልን ለማተም ኢንክ ጀት ፈሳሽ ቀለም የሚጠቀም ሲሆን ሌዘር ጄት ደግሞ ቶነር ይጠቀማል። ሌዘር ማተሚያዎች ተወዳዳሪ የሌለው የማተም ፍጥነት፣ ጉልህ ምስሎችን ማተም እና የተሻለ የህትመት ጥራት አላቸው። ስለዚህም ለመጠነ ሰፊ እና ብዘት ላለው ህትመት እንዲሁም ፕሮፌሽናል የህትመት አጨራረስ ለሚጠይቁ ቢዝነሶች የሚስማማ ነው።

የማተሚያ ታምቡር ምንድን ነው?

ታምቡር ቶነርን ወደ ወረቀት ያስተላልፋል። የሌዘር ማተሚያ ቶነሩን “ ፎቶ ሴንሲቲቭ ድረም” ወደተባለው የታምቡሩ አካል ውስጥ ወደሚገኘው ማስተላለፊያ በማስቀመጥ ቶነሩን በሙቀት እና በግፊት ወረቀቱ ላይ በማስቀመጥ ፊደሎች እና ምስሎችን ያትማል።

ምላሽ ይስጡ

Your email address will not be published. Required fields are marked *